Lyrics

ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና አንድን መፅሐፍ ውስጡን አይተው ሳያጠኑ ቢፈርዱበት ያሳዝናል በሽፋኑ ለማስመሰል አልችል ብዬ ስላቃተኝ ሌላ አደለም የኔው ጠላት እራሴው ነኝ ከሰው ጋር አብሬ ለመኖር ለጊዜው ማስመሰል ባልችልም እራሴን እስከማውቀው ድረስ ያን ያህል ክፉም አደለሁም ግልፅነት እራሴን መሆኔ ቢለየኝ ሃዘኔ ያበቃል ብከፋም በሰው ቂም አልይዝም የልቤን ፈጣሪ ግን ያውቃል ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው ማስመሰል አልችልም አውቃለው ልነጠል ግዴለም ልታገስ እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው ማስመሰል አልችልም አውቃለው ልነጠል ግዴለም ልታገስ እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው ማስመሰል አልችልም አውቃለው ልነጠል ግዴለም ልታገስ እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና ግና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ገባኝ አሁን ገና ገባኝ አሁን ገና ከሰው ጋር ለመኖር አቋራጭ ጎዳና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ማስመሰል መሆኑን እያደረ ገና ሰው ቀርቤ ሰው ሲርቀኝ ሳላስበው ብዙ ጊዜ ግልጽነቴን እረግማለው የገባኝን ከመናገር ስለማላርፍ ክፉ ሆኖ ስሜ ገብቷል በሰዎች አፍ ብቻውን ይኖር ዘንድ በምድር የሰው ልጅ እንዴት ይቻለዋል ጓዳዬን ዘግቼ አልቀመጥ ይህ ልቤ ሰው ይናፍቀዋል ሰው ራቀኝ ተቀየመኝ ብዬ በፀፀት እራሴን አልቀጣም ግድ የለም እምነቴ በሱ ነው አንድ ቀን ቢጤዬን አላጣም ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው ማስመሰል አልችልም አውቃለው ልነጠል ግዴለም ልታገስ እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ ሁሉንም በሱ ላይ ትቻለው ማስመሰል አልችልም አውቃለው ልነጠል ግዴለም ልታገስ እውነቱን እስከሚያውቁት ድረስ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out