Lyrics

እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው እርግፍ አረግሽው ገፋሽው ልቤን ጎዳሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው እርግፍ አረግሽው ጎዳሽው ልቤን ገፋሽው እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው ልጠይቅሽ ተጏዥ ነው ስንቅ የለው ጏዝም የለው ጭኖታል ፈረሱን ልብ አድርገሽ ይሄንን እንቆቅልሽ በይ አስበሽ ድረሺበት መልሱን ተጠይቀሽ መተንተን ካቃተሽ ከከበደሽ የፍቅር ጨዋታው ካላወቅሽው ካጣሽው ሚስጥሩን ሀገር ስጪኝ እንግዲ እኔ ልፍታው እድሜ ላንቺ ካሳብ ምን አጥቼ ከሰጠሺኝ አስኪ ላውጠንጥነው በይ ልንገርሽ ፈርሱም ነገርሽ ስንቁም ፍቅርሽ ተጏዡም ልቤ ነው በይ ልንገርሽ ፈርሱም ነገርሽ ስንቁም ፍቅርሽ ተጏዡም ልቤ ነው በይ ደና ሁኚ መቼም አይገባሽ የሰው ፍቅር እንግዲ እኔም ካንቺ ማደሩ ሲያምረኝ ይቅር በቃኝ አልኩኝ ስለሰለችኝ መጎትጎቱ እስኪ ልየው ይሻለኝ እንደው መለየቱ ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ ዛሬስ የነገር ኑሮ ሰለቸኝ ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅም የለኝ ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ ተስፋ ቢስ ሆኖ መኖር ሰለቸኝ ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅም የለኝም እርግፍ አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው እርግፍ አረግሽው ገፋሽው ልቤን ጎዳሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው ተወት አረግሽው ጎዳሽው ልቤን ጎፋሽው ተወት አረግሽው ረሳሽው ልቤን ጎዳሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ከመውደድሽ አሳነሽው ተስፋ አንዳልሰጠሽው ፍቅርን ነስተሽ አበረርሽው የሚገባሽ የሚሰማሽ መስሎኝ በቁም ነገር ስተርክ መዉደዴን ላይሆንልኝ ጊዜዬን ጨረስኩት ስዘረግፍ አውጥቼው የሆዴን የሰው ነገር ትረጅያለሽ እያልኩ የሃሳቤን እየዘረዘርኩኝ ስለ ፍቅር የማውቀውን ያህል በምሳሌ ብዙ ተናገርኩ አወጋሁት ተጫወትኩ እስካሁን ተናገርኩት አለቀ ነገሬ በኔ በኩል ልሂድ ጨርሻለው አሰናብቺኝ ሩቅ ነው ሀገሬ በኔ በኩል ልሂድ ጨርሻለው አይምሽብኝ ሩቅ ነው ሀገሬ በይ ደና ሁኚ መቼም አይገባሽ የሰው ፍቅር እንግዲ እኔም ካንቺ ማደሩ ሲያምረኝ ይቅር በቃኝ አልኩ ስለሰለቸኝ መጎትጎቱ እስኪ ልየው ይሻለኝ እንደው መለየቱ ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ ዛሬስ የነገር ኑሮ ሰለቸኝ ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ ያንታለ ገልግለኝ ያንታለ መረረኝ አቅምም የለኝ ወትሮም ላይቀናኝ ፍቅር ሰው ወድጄ የቁም ስቃይ አየሁ በገዛ እጄ ተስፋ ቢስ ሆኖ መኖር ሰለቸኝ ያንታለ መረረኝ ያንታለ ገልግለኝ በቃ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out