Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Michael Belayneh
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Michael Belayneh
Songwriter
PRODUCTION & ENGINEERING
Michael Belayneh
Producer
Lyrics
የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንዳለም ዳርቻ እንደርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንዳለም ዳርቻ እንደርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
እንደ ፅጌሬዳ እንደ አደይ አበባ
እንደ ከርቤ ብርጉድ እንደሎሚ ሽታ
አበባ እንዳየ ንብ እኔ እወድሻለሁ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ሂወቴ ነው
አፈር መሬት ትቢያ እንደሚበላው
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው
የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንዳለም ዳርቻ እንደርቀቱ
አይኖችሽም ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
አኔ እወድሻለሁ እንደማታ ጀምበር
ያለም ቋንቋ አይበቃ ቢወራ በነገር
ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አእላፍ ለሊት
ሚሊዮን መሰለኝ ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
አበባ እንዳየ ንብ እኔ እወድሻለሁ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
እንደተወርዋሪ ኮኮብ የማልጠግብሽ
ስወድሽ ስወድሽ ስወድሽ ስወድሽ
የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንዳለም ዳርቻ እንደርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ውድ እወድሻለሁ
Lyrics powered by www.musixmatch.com