Lyrics

አካሌ ሸግዬ ነይ በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ አካሌ ሸግዬ ነይ ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ እንደምን አድረሻል አንቺ አመለ ኩሩ አማላይ ጠፋልሽ ባገር በመንደሩ የማብሰልሰል ሚስጥር የሃሳብ ሹክሹክታ መወያየት ሆኗል ገጥሞ ከትዝታ መወያየት ሆኗል አዬ ገጥሞ ከትዝታ የትከሻዬ ጌጥ የጫንቃዬ ጌታ የዕምሮዬ ደባሽ ሸክሜ የትዝታ ከየት ያደርሰኛል እግሬስ ብሄድበት እታትረው ይዤ በትዝታ አቀበት እታትረው ይዤ አዬ በትዝታ አቀበት አካሌ ሸግዬ ነይ ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ አካሌ ሸግዬ ነይ በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ ተራመጅ በልቤ በለመድሽው መንገድ ያንቺማ ትዝታሽ በፀብ አይታገድ ቢፈርደኝ ምናለ ዳኛ ተሰይሞ ቂመኛው ልቧማ አጠቃኝ አድሞ ቂመኛው ልቧማ አዬ አጠቃኝ አድሞ ፀብ ተራዱኝ አልል ወይ አላድብ ከሰው እኔስ ያንቺን ፍቅር ወዴት ልካሰሰው ድረሽ ልቀበልሽ እጆቼን ዘርግቼ አልካስ በዳኛ አንቺን ረትቼ አልካስ በዳኛ አሄ አንቺን ረትቼ አካሌ ሸግዬ ነይ በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ አካሌ በዳመናው ላይ ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ ከፍቅርሽ ማቅ ወስዶ ልቤን ምን ቀበረው ትዝታን ጎዝጉዞ ሲያስብሽ ያደረው እደርሳለሁ እንጂ በየበራበሩ አንቺ ካልተገኘሽ ምን ሊያምር ነገሩ አንቺ ካልተገኘሽ አዬ ምን ሊያምር ነገሩ የለሽ ካጠገቤ አይሎ ትዝታው ይማፀንሽ ጀመር ምሶሶና ዋልታው ውበትሽ ተወርቶ ሙግት ተነስቶበት ተወራርጄአለሁ እንዳልረታበት ተወራርጄአለሁ አዬ እንዳልረታበት ይቅር ለምስክር እርቄ መሄዴን በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out