Lyrics
ምንቀዉጠዉ ዛሬ አለን እና
ጃኖዬን ለበስኩት እና ደመቅመቅ
ደመቅመቅ ብዬ ልታይ ለሷ እናም
ትመጣለች እመቻት እና እስክታም
ትመታለች እዚሁ ከኔጋ ቆይታም
ትሄዳለች ሲመሽ ከኔጋ
ሲመሽ ከኔጋ እንደዉ ከኔጋ
ሲመሽ ከኔጋ እንደዉ
ቆንጅዬም ታውቃለች ዓይታም አርቃ
እዩአት ታምራለች እጥርጥር ለብሳ
መቀነቱን ለስራ እስክስ ስትመታ
እኔም መሰልኩኝ ያገር ሰው በሷ
ያገር ሰው ያገር ሰው በሷ እንደዉ
ያገር ሰው ያገር ሰው በሷ
ያገር ሰው ያገር ሰው በሷ
ያገር ሰው
ረጋ ብሎ መደሰት ዘዴ እዳሉትም
የሷን ዉድ በሀሪ ስላየሁትም
በድባብ ክት ልዩ ቀለም ስላጀበችኝ
ረጋ ብሎ መደሰት ዘዴ ሲሆነኝ አየች
ነቅነቅ ብሎ መዉረግረግ እስኪያምራት እሷን
ሳላዉቃት ስላየቺኝ ሳያት እንዳዉቃት
ከንፈር ነክስ ለቃላት ሀሳብ ተይዛ
ልትናገር አማራት ውበት አፍዛ እሷ
ዐይኗ ብዙ ሲናገር ልክ እንደ ጥርሷ
እኔም ሳቋን ላሳድ ጊዜ ወረፋ
ይዤ ከሷ መደሰት ነዉ ክብር በለዛ
ካፋዋ ቃላት መለሰች ፈገግታን ከፍላኝ
ረጋ ብሎ መደሰት ዘዴ እንዲሆነን
ባዲስ የጥንት ሙዚቃ ብንነቃነቅ
ረጋ ብሎ መደሰት ዘዴ እንዲሆነን
ባዲስ የጥንት ሙዚቃ ብንነቃነቅ
ይዛኝ እኔን ከሄደችም ምስጠቷ ጠርቷት
ረጋ ብሎ መደሰትም ጉጉት ላይ ጥላት
ይዛኝ እኔን ከሄደችም ምስጠቷ ጠርቷት
ረጋ ብሎ መደሰትም ጉጉት ላይ ጥላት
ሠላም ድባብ ለታይታ ሳይሆን ለሁሌም
ደስታሽ ሲሆን አላማዉ ነገም ለዛሬም
ግራ ሳይገባሽ ቀኝሆኜሽ አንቺም ልብ አለሽ
የኔም ይቆይ ካንቺ ይሁን ጎኔን ከመለሽ
የኔም ይቆይ ካንቺ ይሁን ጎኔን ከመለሽ
የኔም ይቆይ ካንቺ ይሁን ጎኔን ከመለሽ
የኔም ይቆይ ካንቺ ይሁን ጎኔን ከመለሽ
የኔም ይቆይ ካንቺ ይሁን ጎኔን ከመለሽ
ምንቀዉጠዉ ዛሬ አለን እና
ጃኖዬን ለበስኩት እና ደመቅመቅ
ደመቅመቅ ብዬ ልታይ ለሷ እናም
ትመጣለች እመቻት እና እስክታም
ትመታለች እዚሁ ከኔጋ ቆይታም
ትሄዳለች ሲመሽ ከኔጋ
ሲመሽ ከኔጋ እንደዉ ከኔጋ
ሲመሽ ከኔጋ እንደዉ
Writer(s): Fikru Sema
Lyrics powered by www.musixmatch.com