Lyrics

መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፈን (በሚለው ዘፈን) በዕንባ ታጥበን ነበር ስትሄድ ተቃቅፈን (ስትሄድ ተቃቅፈን) መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው (መቅረትክን አላምነው) ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው ኣሄ ሰው ሲያየኝ የተሽኮረመምኩት ኣሄ በዘፈን ማልቀስ የጀመርኩት ኣሄ የፍቅር ደብዳቤ የፃፍኩት ባንተ ነው ሁሉንም የሆንኩት ካንተ ጋር በምሽት ደምቀናል ካንተ ጋር በዝንብ ታጥበናል ካንተ ጋር ተጣልተን ታርቀናል ካንተ ጋር ሁሉንም ሆነናል በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው መለያየት ሞት ነው በሚለው ዘፈን (በሚለው ዘፈን) በዕንባ ታጥበን ነበር ስትሄድ ተቃቅፈን (ስትሄድ ተቃቅፈን) መሄድህን እንጂ መቅረትክን አላምነው (መቅረትክን አላምነው) ዛሬ ነገ ሳትል ፍቅሬ ሳልሞትብህ ብትመጣልኝ ምነው ኣሄ ፀሀይን ሲነጋ ምሞቃት ኣሄ ጨረቃን ላይኔ ምናፍቃት ኣሄሄ አበቦች ያልኩት ማማራቸው ያኔ ነው ካንተ ጋር ሳያቸው ካንተ ጋር አለም ትሞቃለች ካንተ ጋር ቀኔ ትዋባለች ካንተ ጋር ሁሉም ደስ ያሰኛል ካንተ ጋር ሺ ዘመን ያንሰኛል በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው በላኸው አንጀቴን በላኸው እመጣለው ብለህ ሄደህ የቀረኸው
Writer(s): Eyubel Berhanu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out