Lyrics

ትዝታሽ ዘወትር ወደ እኔ እየመጣ እፎይ የምልበት ህይወቴ ጊዜ አጣ እፎይ የምልበት ህይወቴ ጊዜ አጣ ሆዴን ልናዘዘው ለዘመድ ለባዳ ሆዴን ልናዘዘው ለዘመድ ለባዳ አስተናግዳለሁ የልቤ ውስጥ እንግዳ አስተናግዳለሁ የልቤ ውስጥ እንግዳ የትዝታዬ እናት የእድሌ ባለቤት የትዝታዬ እናት የእድሌ ባለቤት እስኪ ልፈልግሽ የት ነው ያለሽበት እስኪ ልጠይቅሽ የት ነው ያለሽበት አቤት ጭር ማለቱ ከተማው ገጠሩ አቤት ጭር ማለቱ ከተማው ገጠሩ ለተዘጋበት ሰው መገናኛው በሩ ለተዘጋበት ሰው መገናኛው በሩ ምነው ቤቴ በሩ በሌሊት ይንኳኳል ምነው ቤቴ በሩ በሌሊት ይንኳኳል እንቅልፍ የሚነሳ ናፍቆት ከደጅ ቆሟል እንቅልፍ የሚነሳ ናፍቆት ከደጅ ቆሟል ልላክ ማስታዎሻ ይነገረኝ መልሱ ልላክ ማስታዎሻ ይነገረኝ መልሱ የተራበው አይኔ ባሰበት ማልቀሱ የተራበው አይኔ ባሰበት ማልቀሱ የከበረ ድንጋይ መክበሪያው ነው እንቁ የከበረ ድንጋይ መክበሪያው ነው እንቁ እንጉርጉሮ ሆኗል የትዝታ ስንቁ እንጉርጉሮ ሆኗል የትዝታ ስንቁ ያቺን ወፍ አንዳችሁ ላኩልኝ በሰው ያቺን ወፍ አንዳችሁ ላኩልኝ በሰው መድሀኒት ናት አሉኝ ፍቅር ለያዘው መድሀኒት ናት አሉኝ ፍቅር ለያዘው ያቺን ወፍ አንዳችሁ ክንፏን አኑሩልኝ ያቺን ወፍ አንዳችሁ ክንፏል አኑሩልኝ ስበር እኖራለሁ መቼም አላለልኝ ስበር እኖራለሁ መቼም አላለልኝ መቼም አላለልኝ መቼም አላለልኝ መቼም አላለልኝ ስበር እኖራለሁ መቼም አላለልኝ ስበር እኖራለሁ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out