Lyrics

ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ እሞታለሁ ብዬ ስባባ፣ መስከረም ጠባ አቤቱ ማማሩ ወንዙ ሸንተረሩ መስኮች አጊጠዋል በአረንጓዴ ከፈይ ዛፎች አብበዋል በቢጫና በቀይ ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ ወይ አዲስ አበባ ወይ ሃገሬ ወይ ሃገርም እንደሰው ይናፍቃል ወይ ለምን ትላላችሁ ሃገሬ ደጌምድር አንድ አይደለም ወይ የኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ ሰላም ላንተ ይሁን የሃገሬ ወታደር የምታስከብረው የሃገርን ድንበር ሰላም ላንተ ይሁን የሃገሬ ሰርቶ አደር በህብረት ስራህ ሃገር የሚዳብር ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ ሰላም ላንተ ይሁን ኩሩው ገበሬው ያመረትከው ሁሉ እርዝ የሚያረካው ሰላም ላንተ ይሁን የሃገሬ ምሁር የምትታገለው ሁሉም እንዲማር ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ በጠረፍ ያለኸው ወደብ ጠባቂው ሰላም ላንተ ይሁን መርከበኛው በጠረፍ ያለኸው ወደብ ጠባቂው ሰላም ላንተ ይሁን መርከበኛው ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ በመንገድ እርቀት እግርህ የማይረታ በረሃብ በጥም የማትፈታ በመንገድ እርቀት እግርህ የማይረታ በረሃብ በጥም የማትፈታ የምታኮራው የድንበሩ ጌታ የሃገሬ ወታደር ይድረስህ ሰላምታ ኢትዮጵያ እናት ሃገር ማንም አይደፍርሽም በጀግና ልጆችሽ ታጥሯል ድንበርሽ
Writer(s): Emahoy Tsege Mariam Gebru Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out