Lyrics
ስጦታክ ዉርሴ ነዉ ስምህ ማህረጌ
በጥበብ በፍቅር እግርክ ስር አድጌ
ከሰማዪ ጌታ ቀጥሎ ከላይ
የቀናዉ መንገዴ ባንተ አይደለም ወይ
ኣባብዬ
ምክርክ እያቀናኝ
ፍቅርህ ያሳደገኝ
አንተን ያገኝካል እኔን የፈለገኝ
ኣባብዬ
በምንም ሁኔታ ብኖር የትም ስፍራ
ግንጥል ጌጥ ነዉ ስሜ ያላንተ ሲጠራ
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በስም ብቻ አይደለም አባ ኣባትነትህ
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በልቤ አለም ላይ ይኸዉ አቅፌ አኖርኩህ
ስጦታክ ዉርሴ ነዉ ስምህ ማህረጌ
በጥበብ በፍቅር እግርክ ስር አድጌ
ከሰማዪ ጌታ ቀጥሎ ከላይ
የቀናዉ መንገዴ ባንተ አይደለም ወይ
ኣባብዬ
ከመልካምነትህ መልካም አግኝቻለዉ
ከወለደኝ በላይ ለወደደኝ ፍቅርክ አመሰግናለሁ
ኣባብዬ
ወደ አለም ብመጣ ድጋሚ ብፈጠር
አባዬ እንደምልክ እንዳትጠራጠር
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በስም ብቻ አይደለም አባ ኣባትነትህ
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በልቤ አለም ላይ ይኸዉ አቅፌ አኖርኩህ
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በስም ብቻ አይደለም አባ ኣባትነትህ
ፍቅርህ ያሳደገኝ ስለኔ ተጎድተህ
በስም ብቻ አይደለም አባ ኣባትነትህ
Lyrics powered by www.musixmatch.com