Lyrics

ግር አለኝ ነገርሽ ጠፍተሽኝ በአመልሽ እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል ቅር አለኝ ነገርሽ ጠፍተሽኝ በአመልሽ እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል የደበቅኩት ሁሉ ይወጣል ፊቴ ላይ ነገር መያዝ አልችል እኔ ካንገት በላይ በልቡ እየኖረ የሰው ልጅ ቅሬታ ነገር አይደብቅም አይን እንደ በሽታ ሰው አርሶ ካጨደ ዳመናውም ዳምኖ ለፍቶ ያገኘውን ያጣል ወይ ለምኖ አሳድጌው ነበር ፍቅርሽን ኮትኩቼ አልታደልኩም እንጂ ለመብላት አንኩቼ ግር አለኝ ነገርሽ ጠፍተሽኝ በአመልሽ እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል ቅር አለኝ ነገርሽ ጠፍተሽኝ በአመልሽ እንቆቆልሽ መስሎ ጨዋታሽ ከብዶኛል ሁኔታሽ በሙሉ ተለውጦብኛል በጣዕምሽ በለዛሽ በአመልሽ ስኩራራ ምነው መምረር ያዘ የፍቅርሽ ሸንኮራ ልቤ ሲጠብቅሽ በራፉን ከፋፍቶ ሳይመለስ ቀረ ያ ፈገግታሽ ጠፍቶ ሰው አርሶ ካጨደ ዳመናውም ዳምኖ ለፍቶ ያገኘውን ያጣል ወይ ለምኖ አሳድጌው ነበር ፍቅርሽን ኮትኩቼ አልታደልኩም እንጂ ለመብላት አንኩቼ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out