Top Songs By Aster Aweke
Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Aster Aweke
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Aster Aweke
Songwriter
Lyrics
አመለ ጨዋ ሲገኝ የሚበጅ
እንስሳም ይለምዳል እንኳን የሰው ልጅ
መውደድ ሸማኔ ፍቅር አዋቂ
ዘንድሮ አገኘሁ ቃሉን ጠባቂ
ቃሉን ጠባቂ
እንቋጨው እንጀምር እንሂድ መንገዱን
የመዋደዳችንን እንይ ማደሪያውን
መጨረሻውን
የሰማይ ከዋክብት ጨረቃ ኮከቤ
የደስታዬ ምክኒያት የማፍቀር ሰበቤ
ሰበቤ
ይውለብለብ ቅጠሉ ይተራመስ አምባው
ይግተልተል አራዊት ያጉረምርም ተራራው
የፀሐይ የጨረቃ የሰማዩ ድምቀት
የቀስተ ዳመና የሰላም መቀነት
የሰላም መቀነት
አልወራረድም ከእንግዲህ በመልኩ
ጨዋነቱ እንጂ የወንድ ልጅ ልኩ
ወድጄህ ወደኸኝ እንዳትቀር አውቃለሁ
መሽቶ ከጨለመ ስትቆይ እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
አመለ ጨዋ ሲገኝ የሚበጅ
እንስሳም ይለምዳል እንኳን የሰው ልጅ
መውደድ ሸማኔ ፍቅር አዋቂ
ዘንድሮ አገኘሁ ቃሉን ጠባቂ
ቃሉን ጠባቂ
ልናገር ማማርክን ቃላት ልምረጥና
ለሰው ልጅ ለአራዊት ለሠማይ ደመና
ደመና
ከብዙኃን አምባ የሌለው ምጣኔ
ምድር ያበቀለው አላየሁም እኔ
እኔ
ይውለብለብ ቅጠሉ ይተራመስ አምባው
ይግተልተል አራዊት ያጉረምርም ተራራው
የፀሐይ የጨረቃ የሰማዩ ድምቀት
የቀስተ ዳመና የሰላም መቀነት
አልወራረድም ከእንግዲህ በመልኩ
ጨዋነቱ እንጂ የወንድ ልጅ ልኩ
ወድጄህ ወደኸኝ እንዳትቀር አውቃለሁ
መሽቶ ከጨለመ ስትቆይ እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
እፈራለሁ
Writer(s): Aster Aweke
Lyrics powered by www.musixmatch.com